የኢትዮጵያ የTCDI የትምባሆ ቁጥጥር ድረ ገጽ

February 22, 2023 Health Development Gateway
Launch, Program

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣት መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔን ለማጠናከር ከዴቨሎፕመንት ጌትዌይ (Development Gateway: an IREX Venture) ጋር በመተባበብር የኢትዮጵያን የትንባሆ ቁጥጥር ድረ ገጽን- (ethiopia.tobaccontroldata.org) እ.አ.አ ከ2021 ጀምሮ ሲያዘጋጅ ቆይቷል፡፡ ድረ ገጹ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ የካቲት 21 ቀን  2015 ዓ.ም የሚመረቅ ሲሆን ሕግ አውጪዎችና ወሳኔ ሰጪ አካላት ትንባሆ ቁጥጥርን በሚመለከት የሚያስፈልጓቸውን መረጃዎች በአመቺ ሁኔታ ተደራሽ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡ የኢትዮጵያው ድረ-ገጽ ዴቨሎፕመንት ጌትዌይ ከኬፕ ታውን ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ጥናት ክፍል (Research Unit on the Economics of Excisable Products (REEP)) ጋር በመተባበር  ከሚያዘጋጃቸው አገር-ተኮር ከሆኑ ድረ ገጾች መካከል አንዱ ነው፡፡ 

በአሁኑ ሰዓት ከኢትዮጵያው ድረ ገጽ በተጨማሪ የደቡብ አፍሪካ፣ የዛምቢያናናይጄሪያ ድረገጾች ተዘጋጅተው ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ሆነዋል፡፡ በቀጣይ የኬንያና  የዴሞክራቲክ ሪፑብለክ ኦፍ ኮንጎ ድረገጾች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ፡፡ እነዚህ ድረ ገጾች የተዘጋጁት ዴቨሎፕመንት ጌትዌይ ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ባደረገለት የገንዘብ ድጋፍ በሚያስፈጽመው የትምባሆ ቁጥጥር ዳታ ኢኒሼቲቭን (Tobacco Control Data Initiative -TCDI) ፕሮግራም አማካኝነት ነው፡፡ 

የእያንዳንዱ ሀገር የTCDI ድረ ገጽ  በትንባሆ ቁጥጥር ዙሪያ ያሉ የመረጃ ክፍተቶችን በመለየት መረጃዎችን አጠናቅሮ ለፖሊሲ አውጪዎችና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ተደራሽ ያደርጋል፡፡ በድረ ገጾቹ የተካተቱት መረጃዎች የትምባሆ ቁጥጥር ሕጎችን ለማፅደቅ እና አፈፃፀማቸውን ለመከታተል አመቺ ሁኔታን እንደሚፈጥሩ ይታመናል። በመሆኑም የኢትዮጵያው ድረ ገጽ በኢትዮጵያ ትንባሆን ከመጠቀም ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ስጋቶች ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው፡፡ 

የTCDI አስፈላጊነት

 

በኢትዮጵያ የትምባሆ አጠቃቀም ከጎረቤት አገሮች ጋር ሲነፃፀር በአንጻራዊ ሁኔታ ዝቅተኛ ነው ፡፡ ሆኖም ከትንባሆ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ በሳምንት 259 ወንዶች እና 65 ሴቶች የሚሞቱ ሲሆን በአጠቃላይ  በዓመት 16,800 ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ (Naghavi, M, et al. 2017)፡፡ የትምባሆ ፍጆታ በዓለም ዙሪያ እየቀነሰ ቢሆንም ከፍተኛ የአጫሾች ቁጥር ጭማሪ በአፍሪካ ይከሰታል ተብሎ ይጠበቃል (Africa’s Tobacco Epidemic, TobaccoTactics, 2021)፡፡ በኢትዮጵያ ሲጋራዎች አሁንም በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኙ በመሆናቸው ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ በሌላ በኩል  በአጠቃላይ እንደሌሎች አፍሪካ አገራት የተለያዩ የገቢ መጠኖች እየጨመሩ ይገኛሉ፡፡  አገሪቷ ብዙ ወጣቶች አሏት። የትምባሆ ቁጥጥር ፖሊሲዎች እንዳይፀድቁና ተግባራዊ እንዳይደረጉ የትምባሆ ኢንዱስትሪው ጣልቃ ገብነት እንቅፋት ይፈጥራል፡፡. በተጨማሪም የትምባሆ አጠቃቀም አሉታዊ ተፅእኖዎች ዙሪያ ያለው ግንዛቤ ውስን ነው፡፡ በመሆኑም ከ 15 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸው 3.4 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የትምባሆ ምርቶችን ይጠቀማሉ (2016 Global Adult Tobacco Survey)፡፡ ምንም እንኳን የኢትዮጵያ የሕግ ማዕቀፍ በአፍሪካ ውስጥ በጣም ጠንካራ ከሚባሉት የትምባሆ ቁጥጥር ሕጎች የሚመደብ ቢሆንም አተገባበሩ ተጠናቅሮ መቀጠል አለበት፡፡  ስለዚህ የትምባሆ ጎጂነት ላይ ያለውን  ግንዛቤ በመጨመር እንዲሁም የትንባሆ ቁጥጥር ፖሊሲዎች አፈፃፀምን በማዳበር የትንባሆ ተጠቃሚ ቁጥር አለመጨመሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ 

የኢትዮጵያ የTCDI ቡድን ባካሄድው የዳሰሳ ጥናት ባለድርሻ አካላት በትንባሆ ቁጥጥር ዙሪያ መረጃ የሚፈልጉባቸውን ጉዳዮች ለመለየት ችሏል፡፡ እነዚህም የትምባሆ ቁጥጥር ሕጎች አፈፃፀም ደረጃ  ፣ የትምባሆ ምርቶች  ሕገወጥ ንግድ ፣ ትምባሆ የሚያስከትለው የኢኮኖሚና የጤና ጉዳት፣ የትምባሆ አጠቃቀም ስርጭት ፣ ትምባሆን መጠቀም ስለማቆም ፣ የትምባሆ ግብር እና የትንባሆ ኢንደስትሪ ጣልቃ ገብነት ናቸው፡፡. ይህንን መሰረት በማድረግ ነባር መረጃዎችን በመለየት እንዲሁም በተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ በማሰብሰብ የተለያዩ ጥናቶች ተካሂደዋል፡፡ በመቀጠለም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ውሳኔ ሰጪ አካላት የትምባሆ ቁጥጥር ፖሊሲዎችን እንዲያጠናክሩ ድጋፍ የሚያደርግ እንዲሁም ስለትንባሆ ግንዛቤ የሚፈጥር ድረ ገጽ ተዘጋጅቷል፡፡ 

 

‹‹አሁን ያለውን የትምባሆ ቁጥጥር ሕግ ተግባራዊነት ማረጋገት ቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ጠንካራ ሕግ አላት፡፡ ሕጉ እንደ ሆስፒታሎች ያሉ ቦታዎችና ቡና ቤቶች ከጭስ ነፃ መሆን እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ ነገርግን ይህ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አልሆነም [….] ሕጉ የሚፈቅድው ሃያ አንድ ዓመት ነው፤ ግን በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች  የትምባሆ ምርቶች ሲገዙ እናያለን፡፡ ሕጉ ሙሉ በሙሉ እየተተገበረ አይደለም ፡፡ ”

- የመንግስት ኃላፊ

የTCDI ኢትዮጵያ ድረ ገጽ

የTCDI ኢትዮጵያ ድረ ገጽ (ethiopia.tobaccontroldata.org) የትምባሆ ቁጥጥርን ለማጠናከርና የሕብረተሰብ ጤናን ለማረጋገጥ ለመንግስት አካላት  ፣ ለሲቪል ማህበረሰቡ ፣ በምርምር ሥራ ውስጥ የሚገኙትን ጨምሮ በአጠቃላይ  ህዝብ ውስጥ ላሉ ባለድርሻ አካላት ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል፡፡ ድረ ገጹ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ምንጮችን መሰረት አድርጎ ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ ሁኔታ መረጃዎችን አቅርቧል፡፡ ግራፎችን ፣ ስዕላዊ መግለጫዎችንና የተለያዩ አገራትን መልካም ተሞክሮቆችን ያካተተ ሲሆን እውነታዎችን ከሚነገሩ የሃሰት መረጃዎች ጋር በማነፃፀር አቅርቧል፡፡ በዚህም መሰረት ደረ ገጹ ከላይ የተጠቀሱት 7 ጉዳዮች ላይ አተኩሯል፡ –  የትምባሆ ቁጥጥር ሕጎች አፈፃፀም ደረጃ  የትምባሆ ምርቶች  ሕገወጥ ንግድ ትምባሆ የሚያስከትለው የኢኮኖሚና የጤና ጉዳት፣ የትምባሆ አጠቃቀም ስርጭት ትምባሆን መጠቀም ስለማቆም የትምባሆ ግብር እና የትንባሆ ኢንደስትሪ ጣልቃ ገብነት፡፡ ፕሮግራሙ ተግባራዊ በሚደረግበት ጊዜ ውስጥ አዳዲስ መረጃዎቸን በማካተት የድረ ገጹን ወቅታዊነት ለማረጋገጥ ጥረት ይደርጋል፡፡ 

የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ የተሰበሰበባቸው የተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች

ከነዚህ ሰባት ጭብጦች ውስጥ የትምባሆ ቁጥጥር ሕጎችን አፈጻፀም የሚመለከተው ገጽ በዋነኝነት ከመጀመረያ ደረጃ ምንጮች በተሰበሰቡ መረጃዎች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ጤና ትምህርት ቤት ምሁራን የሚመራው የጥናት ቡድን የትምባሆ ማስታወቂያንና  የሽያጭ ቦታዎችን ከትምባሆ ጭስ ነፃ ማድረግ ላይ ትኩረት ያደረግ ጥናት አካሂዷል፡፡   ጥናቱ በኢትዮጰያ 10 ከተሞች ውስጥ ተካሂዷል፡፡ ከተሞቹ አዲስ አበባ ፣ አዳማ ፣ አሶሳ ፣ ባህር ዳር ፣ ድሬዳዋ ፣ ጋምቤላ ፣ ሀራሪ ፣ ሀዋሳ ፣ ጂግጂጋ እና ሰመራ ናቸው፡፡ ጥናቱ ሳይንሳዊ ደረጃውን የጠበቀ የመረጃ አሰባሰብ መሳሪያዎችን የተጠቀመ ሲሆን መረጃዎቹን የሰበሰቡት በጉዳዩ በቂ ስልጠና ያገኙ መረጃ ሰብሳቢዎች ናቸው፡፡ በጥናቱ 1,468 የትንባሆ ሽያጭ ቦታዎች ተካተዋል፡፡ እነዚህ የሽያጭ ቦታዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ – ሱፐር ማርኬቶች ፣ የጫት ሱቆች ፣ የሸቀጣሸቀጥ መደብሮች ፣ አነስተኛ ሱቆች ፣ መደበኛ ሱቆች ፣ ቋሚ ኪዮስኮች ፣ የጎዳና ሻጮች እና ምግብ እና የመጠጥ አከፋፋዮች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሌላ 1,378 የእንግዳ ማረፊያ ሥፍራዎች  (ማለትም ሆቴሎች ፣ ምግብ ቤቶች ፣ ቡና ቤቶች ፣ ቡና ቤቶች እና ምግብ ቤቶች ፣ ካፌ እና ምግብ ቤቶች ፣ ስጋ ቤቶች እና የምሽት ክለቦች/ላውንጆች) ተካተዋል፡፡   በተጨማሪም በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ 144 የእንግዳ ማረፊያ ስፍራዎች ውስጥ የPM 2.5 ክምችትን በመመዘን የአየር ጥራትን ለመለካት ተችሏል፡፡. የትንባሆ ቁጥጥር ሕጉን ለመተግበር ያሉትን አመቺ ሁኔታዎችንና ተግዳሮቶችን ለመመርመር በፌደራልና በክልል ከሚገኙ አግባብነት ካላቸው 41 የትምባሆ ቁጥጥር ባለድርሻ አካላት ጋር ጥልቀት ያላቸው ቃለ-መጠይቆች ተካሂደዋል ፡፡ 

የጥናቱ ቡድን በአሁኑ ጊዜ በመረጃ ትንተና እና በሪፖርት ጽሑፍ ሥራ ላይ  ይገኛል፡፡ ግኝቶቹን የያዘው ሪፓርት እ.አ.አ. በመጋቢት 2023 ውስጥ ይሰራጫል፡፡ እነዚህም ግኝቶች በሂደት በድረ ገጹ ውስጥ ይካተታሉ፡፡ የዚህ ጥናት ውጤት የትንባሆ ቁጥጥር አፈፃፀምን ለማጠናከር አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት ይታመናል፡፡

የዝግጅት ሂደት

የTCDI ኢትዮጵያ ድረ ገጽ ከመዘጋጀቱ በፊት የTCDI ቡድን አሁን ያለውን መረጃ እና የባለድርሻ አካላትን ፍላጎቶች ከትምባሆ ቁጥጥር ማህበረሰብ ቁልፍ አባላት ጋር  ቃለ-መጠይቆች በማድረግ ገምግሟል፡፡ የድረ ገጹ የቴክኒክ ስራ ከመጀመሩ በፊት እ.ኤ.አ. ሰኔ 4 ቀን 2021 በተካሄደው አውደ ጥናት  በግምገማው የተገኙ ውጤቶች በባለድርሻ አካላት ተረጋግጠዋል፡፡ ድረ ገጹ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣንን ጨምሮ በኢትዮጵያ ቁልፍ ከሆኑ የትምባሆ ቁጥጥር ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመመካከር ነው (የባለድርሻ አካላትን እና አጋሮቻችንን ሙሉ ዝርዝር እዚህ ማግኘት ይችላሉ)፡፡ የመነሻ ሃሳቦችን እና የድረ ገጹን ዲዛይኖች ለባለድርሻ አካላት በማጋራት አስተያየቶች ተሰባስበዋል፡፡ በመጨረሻም ለዋና ዋና ባለድርሻ አካላት በህዳርና በጥር ወራት የሃሳባ ማሰባሰቢያ ጊዜ በመመደብ የተሰጡ ሃሳቦች እንደአግባብነታቸው እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡ 

አጋር ተቋማት

የየኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን (EFDA) በፈቃድ አሰጣጥ፣ በምርመራ፣ በምዝገባ ፣የላቦራቶሪ ምርመራ በማድረግ ፣ በድህረ-ግብይት ክትትል ፣ በማህበረሰብ ተሳትፎ እና ወቅታዊ  መረጃን በማቅረብ የሕብረተሰብ ጤናን የመጠበቅ እና የማረጋገጥ ኃላፊነት የተሰጠው የመንግሰት ድርጅት ነው፡፡ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባፀደቀው አዋጅ ቁጥር 1263/2021  የተቋቋመ የፌዴራል መንግሥት ተቋም ሲሆን ዋናው መስሪያ ቤት አዲስ አበባ ይገኛል፡፡

EFDA ተጠሪነቱ ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር  ነው፡፡ ትንባሆን በሚመለከት ምርትን ፣ ማስመጣትን ፣ ወደ ውጭ መላክ ፣ ማሰራጨት ፣ አጠቃቀምን ፣ ይዘትን ፣ የመረጃ መግለጫዎችን ፣ ማሸጊያዎችንና ስያሜዎችን የመቆጣጠር ሃላፊነት አለበት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአለም ጤና ድርጅት ኮቬንሽንን ( Framework Convention on Tobacco Control (FCTC)) ተግባራዊ ለማድረግ ከተለያዩ ሴክተር መስሪያቤቶች ጋር በቅንጅት ይሰራል:: ከትንባሆ ጋር በተያያዘ ለሚነሱ የመረጃ ፍላጎቶች እንደ መረጃ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፡፡ ተቋሙ ትንባሆን በመጠቀም የሚከሰቱ  ከባድ ጉዳቶችን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን በማጠናቀር የትንባሆ ቁጥጥር ሥራን ይመራል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ: –  www.efda.gov.et

ዴፈሎፕምነት ጌትዌይ (Development Gateway: an IREX Venture) –  ( DG )

ዴቨሎፕመንት ጌትዌይ ለአለም አቀፍ ልማት መረጃን ተደራሽ በማድረግና ዲጂታል መፍትሄዎችን ለመስጠት የሚሰራ ተቋም ነው፡፡ ተቋማት መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔ ማስተላለፍ እንዲችሉ እገዛ ያደርጋል፡፡ ለዚህም መረጃ መሰብሰብና መተንተን የሚያስችሉ የተለያዩ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን በመፍጠር መረጃን የመጠቀም አቅምን ያጎለብታል፡፡ እ.አ.አ ከ2000 ጀምሮ በተለያዩ አለም ክፍሎች በሚገኙት 5 ዋና ዋና ሃቦች ውጤታማና አሳታፊ ተቋማትን ለመፍጠር መረጃን፣ ቴክኖሎጂን እና ማስረጃዎችን በማጠናቀር ለተጠቃሚዎች የሚያቀርብ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው።  ለተጨማሪ መረጃ:  www.developmentgateway.org.

Share

Related Posts

Stakeholder, Where Art Thou?: Three Insights on Using Governance Structures to Foster Stakeholder Engagement

Through our Tobacco Control Data Initiative (TCDI) program and its sister program Data on Youth and Tobacco in Africa (DaYTA), we have learned that creating governance structures, such as advisory boards or steering committees, is one approach to ensuring that digital solutions appropriately meet stakeholders’ needs and foster future stakeholder engagement. In this blog, we explore three insights on how governance structures can advance buy-in with individual stakeholders while connecting them to one another.

July 16, 2024 Health, Process & Tools
Raising Awareness on World No Tobacco Day 2024: DaYTA/TCDI’s Work on Tobacco Industry Interference

As tobacco companies have aggressively deployed creative strategies to market retail nicotine and tobacco products at children and adolescents, it is imperative that tobacco control stakeholders have access to timely and high-quality data to inform robust policies, regulations, and enforcement mechanisms.

May 31, 2024 Global Data Policy, Health
DG’s Tobacco Control Data Initiative: Reflecting on the First Four Years (Part 1)

As we reach the end of the first four years of TCDI, we reflect on what we’ve accomplished and take stock of lessons we learned while sharing tobacco control data with officials who are monitoring and passing tobacco control legislation in Africa while working in civil society, academia, and government.

February 6, 2024 Health